ኢሳይያስ 32:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፤ ልቡም ዐመፅን ያደርግ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ይበትን ዘንድ፥ የተጠማችንም ነፍስ ባዶ ያደርግ ዘንድ ከንቱን ያስባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰነፍ ስንፍናን ይናገራል፤ አእምሮው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበትን አድራጎት ይፈጽማል፤ በእግዚአብሔርም ላይ የስሕተት ቃል ይናገራል፤ ለተራበ ምግብ ይከለክላል፤ ለተጠማ ውሃ አይሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍ ግን የስንፍናን ነገር ይናገራል፤ ልቡም በጌታም ላይ ስህተትን ለመናገር፥ የተራበችውንም ሰውነት ረሃቡን እንዳያስታግስ፥ የተጠማም ሰው ጥሙን እንዳይቆርጥ በደልን ለመሥራት ክፋትን ያቅዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኞች የሞኝነትን ንግግር ይናገራሉ፤ አእምሮአቸውም በደልን ያሤራል፤ ስለ እግዚአብሔር ስሕተተኛ ንግግርን በማሠራጨት ክሕደትን ያስፋፋል። የተራቡትን አያጠግቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፥ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስህተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል። |
መበለቶች ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ የሙት ልጆችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሃውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ ወዮላቸው!
ቍጣዬን በኀጢአተኛ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፤ ይማርኳቸውና ይበዘብዙአቸው ዘንድ፥ ከተሞችንም ይረግጡአቸውና እንደ ትቢያ ያደርጓቸው ዘንድ ሕዝቤን አዝዛለሁ።
በምድር ጽድቅን የማይማርና መልካምን የማያደርግ ኃጥእ አልቆአልና፥ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኀጢአተኛን ያስወግዱታል።
እርሱ ግን ጠቢብ ነው፤ ክፉንም ነገር በላያቸው ያመጣል፤ ቃሉንም አይመልስም፤ በክፉዎችም ሰዎች ቤት ላይ በከንቱ ተስፋቸውም ላይ ይነሣል።
በድለናል፤ ዋሽተናልም፤ አምላካችንንም መከተል ትተናል፤ ዐመፃን ተናግረናል፤ ከድተንሃልም፤ የኀጢአትንም ቃል ፀንሰን፤ ከልብ አውጥተናል።
እግሮቻቸውም ለተንኮል ይሮጣሉ፤ ደምን ለማፍሰስም ይፈጥናሉ፤ ሰውን ለመግደል ይመክራሉ፤ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
ሰው ሁሉ ክፉና በደለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመፅን ይናገራልና፥ ስለዚህ ጌታ በጐልማሶቻቸው ደስ አይለውም፤ ለሙት ልጆቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያ ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁን?
የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ የተሰማራችሁበት መልካሙ መሰማርያ ባይበቃችሁ ነውን? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ ባይበቃችሁ ነውን?
ድሃውን በብር፥ ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ፥ በእህላችንም ንግድ እንድንጠቀም ሰንበት መቼ ያልፋል? የምትሉ እናንተ ሆይ! ይህን ስሙ።”
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
እግዚእብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፤ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።