ኢሳይያስ 30:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅዱስ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን ይኖራል፤ ልቅሶን አልቅሺ፤ ይቅር በለኝም በዪ፤ ልቅሶሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይልሻል፤ ሰምቶሻልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም። ለርዳታ ወደ እርሱ ስትጮኹ እንዴት ምሕረት አያደርግላችሁ! ጩኸትህን እንደ ሰማም ፈጥኖ ይመልስልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖር ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ እግዚአብሔር ርኅሩኅ ስለ ሆነ የእርሱን ርዳታ በመፈለግ በምትጮኹበት ጊዜ ሰምቶ መልስ ይሰጣችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፥ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል። |
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአሦር የተነሣ አትፍራ፤ በበትር ይመቱሃልና፥ የግብፅንም መንገድ ታይ ዘንድ መቅሠፍቴን አመጣብሃለሁና።
ሞት ሰዎችን ዋጠ፤ በረታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር በአፉ ተናግሮአልና።
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
ድሆችና ምስኪኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያገኙምም፤ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፤ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
ያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ፤ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ይልሃል። የዐመፅ እስራትን ከመካከልህ ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ማንጐራጐርንም ብትተው፥
እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ያልፋልና፤ ፀሐይሽ ከዚህ በኋላ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም።
እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤትን አደርጋለሁ፤ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ በውስጥዋ አይሰማም።
የያዕቆብን ዘርና የይሁዳን ዘር አመጣለሁ፤ የተቀደሰው ተራራዬንም ይወርሳሉ፤ እኔ የመረጥኋቸውና ባሪያዎችም ይወርሱአታል፤ በዚያም ይኖራሉ።
ይመጣሉ፤ በጽዮንም ተራራ ደስ ይላቸዋል፤ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ሀገርም ይሰበሰባሉ፤ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይራቡም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድምፅሽን ከልቅሶ፥ ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ ዋጋ ይሆናልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ።
በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።”
እያለቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስሄዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።”
የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፥ የመቅደሱንም በቀል፥ በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን ሀገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።
“በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው ለዘለዓለም ይገዙልኛል፤ በዚያም እቀበላችኋለሁ፤ በዚያም ቀዳምያታችሁን፥ በኵራታችሁንም፥ የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ እጐበኛለሁ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።
ከዚህ በኋላም መላው እስራኤል ይድናሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ፥ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ኀጢአትን ያስወግዳል።
በከሃሊነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የምናስበውንና የምንለምነውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበዙም ዘንድ ሊያጸናችሁ ለሚችል፥
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”