እናንተ የተረፋችሁና መከራ የምትቀበሉ ሆይ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የነገረኝንና የሰማሁትን ስሙ።
ኢሳይያስ 28:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ለዘለዓለም በእናንተ ላይ አልቈጣም፤ የምሕረቴም ድምፅ አያጠፋችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ስለዚህ አንድ ሰው ለዘላለም እህል ሲወቃ አይኖርም። የመውቂያውን መንኰራኵር ቢያኼድበትም፣ ፈረሶቹ አይደፈጥጡትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ነገር ግን ለዘለዓለም አይፈጨውም፤ የሠረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቀውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስንዴና ገብስ ይወቃሉ እንጂ እንዲደቁ አይደረጉም፤ ሠረገላና ፈረስ በላያቸው ላይ ቢነዱም እንኳ እንዲደቁ አይደረጉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንጀራ እህል ይደቅቃልን? ለዘላለም አያኬደውም፥ የሰረገላውን መንኮራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም። |
እናንተ የተረፋችሁና መከራ የምትቀበሉ ሆይ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የነገረኝንና የሰማሁትን ስሙ።
ጥቍሩን አዝሙድ በተሳለች ማሄጃ አያሄድም፤ የሰረገላም መንኰራኵር በከሙን ላይ አይዞርም፤ ነገር ግን ጥቍሩን አዝሙድ በሽመል፥ ከሙኑንም በበትር ይወቃል።
ይህም ደግሞ ድንቅ ምክርን ከሚመክር በግብሩም ገናና ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል። እናንተ ግን ከንቱ መጽናናትን ታበዙ ዘንድ ትሻላችሁ።
እነሆ አዝዛለሁ፤ እህልም በመንሽ እንደሚዘራ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እዘራለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
መባቸውንም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፤ የተከደኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ በየሁለቱም አለቆች አንድ ሰረገላ አቀረቡ፤ ሁሉም እያንዳንዱ አንድ በሬ በድንኳኑ ፊት አቀረቡ።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በምድር ላይ ካልወደቀችና ካልሞተች ብቻዋን ትኖራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬን ታፈራለች።
በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።