ኢሳይያስ 22:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ መከራ ሀገር ይጥልሃል፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ያማረ ሰረገላህንም ያጐሰቍለዋል፤ የአለቃህም ቤት ይረገጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤ አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረት! በዚያ ትሞታለህ፤ የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቅልሎም ያንከባልልሃል፥ ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይወረውርሃል፤ አቤት፥ አንተ የጌታህ ቤት እፍረት! በዚያም ትሞታለህ፥ በዚያም የክብርህ ሠረገላዎች ይቀራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ወደምትሞትበትና ሠረገሎችህም ቆመው ወደሚቀሩበት ቦታ እንደ ኳስ ጠቅልሎ ወደ ሰፊው ሜዳ ይወረውርሃል፤ ለጌቶችህም ኀፍረት ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠቅልሎም ያንከባልልሃል ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይጥልሃል፥ አንተ የጌታህ ቤት እፍረት! በዚያ ትሞታለህ በዚያም የክብርህ ሰረገላዎች ይሆናሉ። |
እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ።
ብዙዎች አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏፏቴ ውስጥ በኀይል እንደሚወርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮኻሉ፤ ያጠፉታልም፤ እነርሱም ከሩቅ ይወርዳሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፥ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው እንደ መንኰራኵር ትቢያም ይበተናሉ።
እነሆ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በኀይል ወርውሮ ይጥልሃል፤ ያጠፋሃልም፤ ልብስህንና የክብር አክሊልህንም ይገፍሃል፤
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”