በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ፥ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ መልካምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። በዐለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ወዳለው ጥላ ነዪ።
ኢሳይያስ 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ቀጫጭን ዘንግ በማጭድ ይቈርጣል፤ ጫፎቹንም ይመለምላል፤ ያስወግድማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመከር በፊት የአበባው ወቅት ሲያልፍ፣ አበባው የጐመራ የወይን ፍሬ ሲሆን፣ የወይን ሐረጉን ተቀጥላ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ የተንሰራፋውንም ቅርንጫፍ ቈራርጦ ያስወግደዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ፥ አበባው ያበበ የወይንም ፍሬ ሲይዝ፥ የወይኑን ዘንግ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ ጫፎቹንም መልምሎ ያስወግዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ዘንግ በማጭድ ይቈርጣል፥ ጫፎቹንም ይመለምላል ያስወግድማል። |
በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ፥ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ መልካምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። በዐለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ወዳለው ጥላ ነዪ።
እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክቡራንን በኀይል ያውካቸዋል፤ ታላላቆችንም በሐሣር ይቀጠቅጣቸዋል፤ ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ።
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።