ኢሳይያስ 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኔምሬም ውኃ ይነጥፋል፤ ሣሯም ይደርቃል፤ በውስጧም ልምላሜ አይገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤ ሣሩ ጠውልጓል፤ ቡቃያውም ጠፍቷል፤ ለምለም ነገር አይታይም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፤ ለጋውም ጠውልጓል፤ ልምላሜውም ሁሉ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኒምሪም ወንዞች ደርቀዋል፤ ምንም ልምላሜ ሳይቀር በአጠገቡ ያለው ሣር ደርቆአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፥ ሣሩም ደርቋል፥ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም። |
ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤሊያሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከሴጎር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃ ደርቋልና።
እሳት በፊታቸው ትበላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋላቸውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእርሱም የሚያመልጥ የለም።
በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ።
ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።