የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
ኢሳይያስ 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከግንዱ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእሴይ ግንድ ቁጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግንድ እንደሚያቈጠቊጥና ከስሩም ቅርንጫፍ እንደሚያበቅል እንዲሁም ከእሴይ (ከዳዊት ንጉሣዊ) ዘር አንድ ንጉሥ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል። |
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
በዚያም ቀን የእሴይ ሥር ይቆማል፤ የተሾመውም የአሕዛብ አለቃ ይሆናል፤ አሕዛብም በእርሱ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
ነገራችን በፊቱ እንደ ሕፃን፥ በደረቅ መሬትም እንዳለ ሥር ሆነ፤ መልክና ውበት የለውም፤ እነሆ፥ አየነው፤ ደም ግባት የለውም፤ ውበትም የለውም።
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
“እነሆ ለዳዊት የጽድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤ ንጉሥ ይነግሣል፤ ያስባል፤ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከረዥሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀንበጥን ወስጄ አኖረዋለሁ፤ ከጫፎቹም አንዱን ቀንበጥ እቀነጥበዋለሁ፤ በረዥምና በታላቅ ተራራም ላይ እተክለዋለሁ።
አባቶቻችሁም በኖሩባት፤ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው፥ የልጅ ልጆቻቸውም ለዘለዓለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘለዓለም አለቃ ይሆናቸዋል።
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።
ኢሳይያስም ደግሞ እንዲህ ብሎአል፥ “የእሴይ ዘር ይነሣል፤ ከእርሱ የሚነሣውም ለአሕዛብ ንጉሥ ይሆናል፤ ሕዝቡም ተስፋ ያደርጉታል።”
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።
ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት፣ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው።