ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
ኢሳይያስ 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋሊም ልጅ ትሸሻለች፤ ላይሳም ትሰማለች፤ አናቶትም ትሰማለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺ! ላይሻ ሆይ፤ አድምጪ! ምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ ስሚ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺ! ላይሻ ሆይ፤ አድምጪ! ምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ መልሺላት! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋሊም ሕዝብ ሆይ! እሪ በሉ! የላይሻም ሕዝብ ሆይ! አድምጡ! የዐናቶትም ሰዎች መልስ ስጡ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ የጋሊም ልጅ ሆይ፥ በታላቅ ድምፅሽ ጩኺ፥ ላይሳ ሆይ፥ አድምጪ፥ አናቶት ሆይ፥ መልሽላት። |
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
በብንያም ሀገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬልቅያስ ልጅ ወደ ኤርምያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል።
እንደ እግዚአብሔርም ቃል የአጎቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወደ አለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፥ “በብንያም ሀገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ፤ የመግዛትና የመውረስ መብቱ የአንተ ነውና፥ አንተ ታላቃችን ነህና፤ ለአንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ።
ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤ የከተማዪቱም ስም አስቀድሞ ሌሳ ነበረ።
አምስቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፤ እንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐርፈው፥ ተዘልለውም ተቀምጠው ነበር፤ በተመዘገበች የርስታቸው ምድርም ቃልን መናገር አልቻሉም፤ ከሲዶናውያንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶርያውያንም ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም።