ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
ኢሳይያስ 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤአለሁ፤ የበሬና የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል እግዚአብሔር። “የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሠቡ እንስሳትን ሥብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል ጌታ። የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይረባኛል? እስከ አሁን ያቀረባችሁልኝ የአውራ በግ፥ የተቃጠለ መሥዋዕትና የፍሪዳ ስብ በቅቶኛል፤ በኰርማና በበግ ጠቦት፥ በአውራ ፍየልም ደም አልደሰትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል? ይላል እግዚአብሔር፥ የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤያለሁ፥ የበሬና የበግ ጠቦት የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም። |
ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
ነገር ግን ጽድቅን እንደሚያደርግ የአምላኩንም ፍርድ እንደማይተው ሕዝብ ዕለት ዕለት ይሹኛል፤ መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ። አሁንም እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም።
የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከቍርባናችሁ ጋር የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፤ ሥጋውንም ብሉ።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
ሕጉን በውጭ አነበባችሁ፤ የታመነም አላችሁት፤ በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ የድኅነት መሥዋዕታችሁንም አልመለከትም።
እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?
ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፣ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፣ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው።
ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።
ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።