ሆሴዕ 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓመት በዓል ቀንና በእግዚአብሔር በዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣ በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓመት በዓል ቀንና በጌታ በዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ለእግዚአብሔር ክብር በተወሰኑት የዓመት በዓላት ምን ታደርጋላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓመት በዓል ቀንና በእግዚአብሔር በዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ? |
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት! ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠውያ አገልጋዮች! ዋይ በሉ፤ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።