በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ሆሴዕ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእህሉ አውድማና የወይኑ መጭመቂያ አላወቃቸውም፤ ወይኑም ጐደለባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእህል ዐውድማዎችና የወይን መጭመቂያዎች ሕዝቡን አይመግቡም፤ አዲሱም የወይን ጠጅ ይጐድልባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውድማውና ወይን ጠጅ መጥመቂያው አይመግባቸውም፥ በመጥመቂያውም ውስጥ አዲስ የወይን ጠጅ ጐድሏል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ከዐውድማችሁ እህልን፥ ከመጭመቂያችሁም የወይን ጠጅን ከቶ አታገኙም፤ አዲስ የወይን ጠጅም አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውድማውና መጥመቂያው አይመግባቸውም፥ ጉሽ ጠጅም ይጐድልባታል። |
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
እርስዋም፥ “ወዳጆች የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ሁሉ ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ምስክርም ይሆኑ ዘንድ አኖራቸዋለሁ፤ የምድረ በዳም አራዊትና የሰማይ ወፎች፥ የምድር ተንቀሳቃሾችም ይበሉታል።
ስለዚህ እህሌን በጊዜው፥ ወይኔንም በወራቱ እወስዳለሁ፤ ኀፍረቷንም እንዳትሸፍን ልብሴንና መጎናጸፊያዬን እገፍፋታለሁ።
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ፣ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው።
በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።