La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሆሴዕ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለሰ​ማይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሰማ​ይም ለም​ድር ይመ​ል​ሳል፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን እኔ እመልሳለሁ፤ ለሰማያት እመልሳለሁ፤ እነርሱም ለምድር ምላሽ ይሰጣሉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለዘለዓለምም ለእኔ እንድትሆኚ አጭሻለሁ፤ በጽድቅና በፍርድ፥ በምሕረትና በጽኑ ፍቅር ለእኔ አጭሻለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ቀን እኔ መልስ አሰጣለሁ፤ እኔ ለሰማያት መልስ እሰጣለሁ፤ ሰማያትም ለምድር መልስ ይሰጣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለዘላለምም ለእኔ እንድትሆኚ አጭሻለሁ፥ በጽድቅና በፍርድ በምሕረትና በርኅራኄ አጭሻለሁ።

Ver Capítulo



ሆሴዕ 2:21
15 Referencias Cruzadas  

ብዙ ዝና​ምና በረዶ ከሰ​ማይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ፥ ምድ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ረ​ካት፥ ታበ​ቅ​ልና ታፈ​ራም ዘንድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጋት፥ ዘርን ለሚ​ዘራ፥ እህ​ል​ንም ለም​ግብ እን​ደ​ሚ​ሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ፥


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “የተ​ተ​ወች” አት​ባ​ዪም፤ ምድ​ር​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አት​ባ​ልም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንቺ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ ምድ​ር​ሽም ባል ታገ​ባ​ለ​ችና አንቺ፥ “ደስ​ታዬ የሚ​ኖ​ር​ባት” ትባ​ያ​ለሽ፤ ምድ​ር​ሽም፥ “ባል ያገ​ባች” ትባ​ላ​ለች።


ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።


ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ይዘ​ረ​ጋሉ፤ ውበ​ቱም እንደ ወይራ፥ ሽታ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ እህ​ል​ንና ወይ​ንን፥ ዘይ​ት​ንም እሰ​ድ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በእ​ርሱ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል መሰ​ደ​ቢያ አላ​ደ​ር​ጋ​ች​ሁም።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።


አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?