ሆሴዕ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነኝ። በቤትአዎንም አገኘኝ፤ በዚያም ከእኔ ጋር ተነጋገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ የሚታወቅበት ስሙ እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሠራዊት አምላክ የመታወቂያው ስሙ እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፥ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርያ ከተመለሰ በኋላ እንደገና በሎዛ ተገለጠለት፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘለዓለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።