ሆሴዕ 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገለዓድ ባይሆንም እንኳ በጌልጌላ መሥዋዕታቸውን የሚሠዉ አለቆች ስተዋል፤ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድንጋይ ክምር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሸሸ፤ እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤ ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአት በገለዓድ አለ፤ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፤ በሬዎችን በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልሞች ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባታችን ያዕቆብ ወደ መስጴጦምያ ሸሽቶ ሄደ፤ እዚያም ሚስት ለማግኘት ሲል የበጎች እረኛ ሆኖ አገለገለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት በገለዓድ አለ፥ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፥ ወይፈኖች በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ። |
ለአንተ ቤት የተገዛሁልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፤ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።
እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ።
በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።