እንግዲህ ኦሪት እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ልትከለክል መጣችን? አይደለም፤ ማዳን የሚቻለው ሕግ ተሠርቶ ቢሆንማ፥ በእውነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተገኘ ነበር።
ዕብራውያን 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊተኛይቱ ያለ ነቀፋ ብትሆን ኖሮ ሁለተኛይቱን ባልፈለገም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጕድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊተኛው ኪዳን ጉድለት ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ነቀፋ የሌለው ሆኖ ቢገኝ ኖሮ ሁለተኛው ቃል ኪዳን ባላስፈለገ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። |
እንግዲህ ኦሪት እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ልትከለክል መጣችን? አይደለም፤ ማዳን የሚቻለው ሕግ ተሠርቶ ቢሆንማ፥ በእውነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተገኘ ነበር።
እንግዲህ ሕዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ወደ ፊት ስለምን ያስፈልጋል?
ዛሬ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ የምትበልጠውን አገልግሎት ገንዘብ አደረገ፤ ለታላቂቱ ሥርዐትም መካከለኛ ሆነ፤ የምትበልጠውንም ተስፋ ሠራ።