La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕብራውያን 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወገ​ና​ቸው ላይ​ደለ ለእ​ርሱ ግን አብ​ር​ሃም ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው፤ እር​ሱም ተስፋ ያለው አብ​ር​ሃ​ምን ባረ​ከው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህ ግን ትውልዱ ከሌዊ ወገን አይደለም፤ ይሁን እንጂ ከአብርሃም ዐሥራት ተቀበለ፤ የተስፋ ቃል የተቀበለውንም ባረከው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህ ሰው ምንም ትውልዱ ከእነርሱ ባይቆጠርም እንኳ ከአብርሃም አሥራትን ተቀብሏል፤ የተስፋ ቃል የተሰጠውን አብርሃምንም ባርኮአል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያ መልከጼዴቅ የሌዋውያን ዘር ባይሆንም እንኳ ከአብርሃም ዐሥራትን ተቀበለ፤ የተስፋ ቃል የተሰጠውን አብርሃምንም ባረከው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ትውልዱ ከእነርሱ የማይቍኦጠረው ግን ከአብርሃም አሥራትን አውጥቶአል፥ የተስፋ ቃል የነበረውንም ባርኮአል።

Ver Capítulo



ዕብራውያን 7:6
16 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ በአ​ንቺ ምክ​ን​ያት መል​ካም ይሆ​ን​ልኝ ዘንድ፥ ስለ አን​ቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ እኅቱ ነኝ በዪ።”


ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


እና​ን​ተም የነ​ቢ​ያት ልጆች ናችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሠ​ራው ሥር​ዐ​ትም የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ናችሁ፤ ለአ​ብ​ር​ሃም፦ ‘በዘ​ርህ የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ይባ​ረ​ካሉ’ ብሎ​ታ​ልና።


አብ​ር​ሃም፥ ዘሩም ዓለ​ምን ይወ​ርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት አይ​ደ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እር​ሱ​ንም በማ​መን በእ​ው​ነ​ተና ሃይ​ማ​ኖቱ ይህን አገኘ እንጂ።


እና​ህም ልጅ​ነት፥ ክብር፥ ኪዳን፥ ሕግና አም​ልኮ ያላ​ቸው፥ ተስ​ፋም የተ​ሰ​ጣ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም፥ “ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ” ብሎ ተስፋ ሰጠው፤ ለብ​ዙ​ዎች እን​ደ​ሚ​ና​ገር አድ​ርጎ ለአ​ን​ተና ለዘ​ሮ​ችህ አላ​ለ​ውም፤ ለአ​ንድ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አድ​ርጎ፥ “ለዘ​ርህ” አለው እንጂ ይኸ​ውም ክር​ስ​ቶስ ነው።


እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።


አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ተ​ነው ጊዜ ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ይሠ​ዋው ዘንድ በእ​ም​ነት ወሰ​ደው።


የሳ​ሌም ንጉሥ፥ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህን የሆነ፥ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብ​ር​ሃም ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሥቶ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ና​ኝቶ ባረ​ከው።


ነገር ግን ታላቁ ታና​ሹን እን​ደ​ሚ​ባ​ር​ከው ያለ ጥር​ጥር ይታ​ወ​ቃል።