ዕብራውያን 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልዩ ልዩ ዐይነት እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን የሚጸናው በጸጋ እንጂ የምግብ ሥርዐት በመጠበቅ አይደለም፤ ይህን ሥርዐት የሚጠብቁት እንኳ በዚህ አልተጠቀሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ መልካም የሚሆነው ልባችሁ በጸጋ ቢጸና ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚኖሩትም እንኳን አልተጠቀሙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና። |
አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፥ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
አንዳንድ ቀን የተከለከለም ለእግዚአብሔር ተከለከለ፤ ዘወትር የተከለከለም ለእግዚአብሔር ተከለከለ፤ የበላም ለእግዚአብሔር በላ፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግነዋል፤ ያልበላም ለእግዚአብሔር አልበላም፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግነዋል።
መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ይሽራቸዋል፤ ሥጋችሁም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ እግዚአብሔርም ለሥጋችሁ ነው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ከእናንተ ወገን የተሳሳተ ሰው ቢኖር በመንፈስ ቅዱስ የጸናችሁ እናንት እንዳትሳሳቱ ለራሳችሁ እየተጠበቃችሁ፥ እንደዚህ ያለውን ሰው ቅንነት ባለው ልቡና አጽኑት።
እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን።
በከንቱ ነገርም የሚያስታችሁ አይኑር፤ በእርሱ ምክንያት በከሓዲዎች ልጆች ላይ የእግዚአብሔር መዓት ይመጣልና።
ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።