La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕንባቆም 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እነሆ፤ እርሱ ታብዮአል፤ ምኞቱ ቀና አይደለም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ ይኖራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ እርሱ ኮርቶአል፥ ነፍሱ በውስጡ ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ትዕቢተኞችን ተመልከት፤ አስተሳሰባቸው ቅን አይደለም፤ ጻድቃን ግን በእምነታቸው ይኖራሉ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፥ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።

Ver Capítulo



ዕንባቆም 2:4
17 Referencias Cruzadas  

ሌባ​ውን ባየህ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ትሮ​ጣ​ለህ፥ ዕድል ፋን​ታ​ህ​ንም ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር አደ​ረ​ግህ።


በዓ​ለም ሁሉ ላይ ክፋ​ትን አዝ​ዛ​ለሁ፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ኀጢ​አት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም ኵራት እሽ​ራ​ለሁ፤ የጨ​ካ​ኞ​ቹ​ንም ኵራት አዋ​ር​ዳ​ለሁ።


በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እው​ነ​ት​ንም ለማ​ድ​ረግ ፍር​ዴን ቢጠ​ብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።


“ጻድቅ በእ​ም​ነት ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከእ​ም​ነት ወደ እም​ነት በእ​ርሱ ይገ​ለ​ጣ​ልና።


ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ እኛም የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ሳይ​ሆን በእ​ርሱ በማ​መ​ና​ችን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ነ​ናል፤ ሰው ሁሉ በኦ​ሪት ሥራ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና።


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።