ዕንባቆም 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ፥ ፊታቸውንም እንደ ምሥራቅ ነፋስ ያቀናሉ፣ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም ለዐመፅ ታጥቀው ይመጣሉ። ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ለዓመፅ ይመጣሉ፥ ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ ያቀናሉ፤ ምርኮኞችን እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሠራዊታቸው ሁሉ የዐመፅ ሥራ ለመፈጸም ይገሠግሣሉ፤ ፊታቸው ከወደ ምሥራቅ እንደሚመጣ ነፋስ ያቃጥላል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ፥ ፊታቸውንም እንደ ምሥራቅ ነፋስ ያቀናሉ፥ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ። |
እኔም እንደምሸመግልና እንደማረጅ፥ እንደ ረዥም ዘንባባም ረዥም ዘመን እንደምኖር፥ እንደ አሸዋም ዘመኔን እንደማበዛ ዐሰብሁ።
መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተዋል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጭንቀትንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
እነሆ እኔ አዝዛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደዚህችም ሀገር እመልሳቸዋለሁ፤ እርስዋንም ይወጋሉ፤ ይይዙአትማል፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይሏቸዋል፦ በምድረ በዳ የሚያስት ጋኔን አለ፤ የሕዝቤ ሴት ልጅ መንገድም ለንጽሕና ወይም ለቅድስና አይደለም።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
ተተክሎስ፥ እነሆ ይከናወንለት ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።”
ነገር ግን በመዓት ተነቀለች፤ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የሚያቃጥልም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱዎች በትሮችዋም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቻቸው።
የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እንዲህም ይሆናል፤ “እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም” ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።
ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
ኢሳይያስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ስለ እስራኤል እንዲህ አለ፥ “የእስራኤል ልጆች ቍጥራቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም የተረፉት ይድናሉ።
ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ልጆች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት ቍጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ።