ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ያለቅሳሉ።
ዕንባቆም 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉን በመቃጥን ያወጣል፥ በመረቡም ይይዛቸዋል፥ በአሽክላውም ውስጥ ያከማቻቸዋል፣ ስለዚህ ደስ እያለው እልል ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉንም በመንጠቆ ያወጣቸዋል፤ በመረቡ ይይዛቸዋል፤ በወጥመዱ ውስጥ ይሰበስባቸዋል፤ በዚህም ይደሰታል፤ ሐሤትም ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉን በመንጠቆ ያወጣል፥ በመረቡ ይጎትታቸዋል፥ በአሽክላውም ውስጥ ያከማቻቸዋል፤ ስለዚህ ደስ ይለዋል፥ ሐሤትም ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓሣ በመንጠቆ እንደሚያዝ ጠላት ሁሉንም ይይዛቸዋል፤ በመረብም እንደሚጐተት ይጐትታቸዋል፤ በማከማቻው ይሰበስባቸዋል፤ ይህን በማድረጉ በደስታ ይፈነጥዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን በመቃጥን ያወጣል፥ በመረቡም ይይዛቸዋል፥ በአሽክላውም ውስጥ ያከማቻቸዋል፥ ስለዚህ ደስ እያለው እልል ይላል። |
ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ያለቅሳሉ።
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አድዳኞችን እልካለሁ፤ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድድኑአቸዋል።
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእጆችህ አጨብጭበሃልና፥ በእግሮችህም አሸብሽበሃልና፥ ሰውነትህም በእስራኤል ምድር ላይ ደስ ብሎአታልና፤
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰበረች፥ ጠፋችም፥ ሕዝቧም ወደ እርስዋ ተመለሱ፤ ሞልታ የነበረች አለቀች ብላለችና፤
የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ! አንተና መላው ኤዶምያስ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።”
ጌታ አግዚአብሔር፥ “እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን እነሆ በላያችሁ ይመጣል” ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል።
እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።
ነገር ግን እንዳናሰናክላቸው፥ ወደ ባሕር ሂድና መቃጥን ጣል፤ መጀመሪያም የሚወጣውን ዓሣ ውሰድና አፉን ስትከፍት እስታቴር ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው፤” አለው።
እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።