በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤
ዘፍጥረት 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃውም ከምድር ላይ እያደር እየቀለለ ይሄድ ጀመረ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጐደለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ ዐምሳ ቀን በኋላም ጐደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውሃው ቀስ በቀስ ከምድር ላይ ቀለለ፥ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጎደለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃው ቀስ በቀስ ከምድር ላይ መጒደል ጀመረ፤ ከመቶ ኀምሳ ቀኖችም በኋላ ውሃው ከምድር ላይ በጣም ጐደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ ውኂውም ከምድር ላይ እያደር እያደር ቀለለ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኂው ጎደለ። |
በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤
ውኃውም እስከ ዐሥረኛው ወር ድረስ ይጐድል ነበር፤ በዐሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ራሶች ተገለጡ።