ከወፎች ሁሉ በየወገናቸው፥ ከእንስሳም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ ከሚሳቡ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በየወገናቸው ከአንተ ጋር ይመገቡ ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ።
ዘፍጥረት 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ። |
ከወፎች ሁሉ በየወገናቸው፥ ከእንስሳም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ ከሚሳቡ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በየወገናቸው ከአንተ ጋር ይመገቡ ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ።
ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ሁሉ ላይ አጠፋለሁና።”
ከንጹሓን ወፎችና ንጹሓን ካልሆኑ ወፎች፥ ከንጹሕ እንስሳ፥ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።