እስራኤልም ዮሴፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
ዘፍጥረት 50:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “ውጣ፤ አባትህንም እንዳማለህ ቅበረው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም፣ “በአስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፦ “ሂድ፥ አባትህን እንዳስማለህ ቅበረው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖንም ይህን ሰምቶ “ቃል በገባህለት መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም፦ ውጣ አባትህንም እንዳማለህ ቅበረው አለው። |
እስራኤልም ዮሴፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
አባቴ ሳይሞት አምሎኛል፤ እንዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር በዚያ ቅበረኝ።’ አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።”
ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ፤ የፈርዖን ሎሌዎችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም ሁሉ፥ የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፤