ዘፍጥረት 49:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ ውስጥ ያለው ዋሻ፣ የመቃብር ቦታ እንዲሆን አብርሃም ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ ከነዕርሻ ቦታው የገዛው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም በከነዓን ምድር ከመምሬ በስተ ምሥራቅ በኩል በማክፌላ የሚገኘው ነው፤ አብርሃም ይህ ዋሻ የሚገኝበትን እርሻ ለመቃብር ቦታ የገዛው ከሒታዊው ከዔፍሮን ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ዋሻ በከነዓን ምድር ከመምሬ በስተምሥራቅ በኩል በማክፌላ የሚገኘው ነው፤ አብርሃም ይህ ዋሻ የሚገኝበትን እርሻ ለመቃብር ቦታ የገዛው ከሒታዊው ከዔፍሮን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት። |
“እኔ በእናንተ ዘንድ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ፤ በእናንተ ዘንድ እንድገዛ የመቃብር ርስት ስጡኝ፤ ሬሳዬንም እንደ እናንተ ልቅበር።”
ልጆቹ ይስሐቅና ይስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።