ዘፍጥረት 49:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳን በጎዳና ላይ እንደሚያደባ እባብ ይሆናል፤ በመንገዱም የፈረሱን ሰኰና እንደሚናደፍ እንደ ቀንዳም እባብ ነው፤ ፈረሰኛውም ወደኋላው ይወድቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣ የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣ የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳን በጐዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል፥ በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ፥ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል፥ ፈረሰኛም ወደ ኋላው ይወድቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሰኛው ሰው ወደኋላው ይወድቅ ዘንድ፥ ዳን እንደ ነዳፊ እባብ ሆኖ፥ በመተላለፊያው መንገድ ላይ የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳን በጕዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል ፈረስኛም ወደኍላው ይወድቃል። |