ዘፍጥረት 49:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይሳኮር መልካም ነገርን ወደደ፤ በተወራራሾቹም መካከል ያርፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይሳኮር፣ በበጎች ጕረኖም መካከል የሚተኛ ዐጥንተ ብርቱ አህያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፥ በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይሳኮር በበጎች መካከል እንደሚተኛ ብርቱ አህያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው በበጎች ጕረኖም መካከል ያርፋል |
ዕረፍትም መልካም መሆንዋን፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን በአየ ጊዜ ምድርን ያርሳት ዘንድ ትከሻውን ዝቅ አደረገ፤ በሥራም ገበሬ ሆነ።
እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የአባቱ ወንድም ልጅ የፎሓ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም በኤፍሬም ተራራ በሳምር ተቀምጦ ነበር።