ዘፍጥረት 46:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት፤ ባላ የወለደቻቸው ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሰባቱ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሰባቱ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። |