እንዲህም ብለው ነገሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕይወቱ ነው፤ እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፤ አላመናቸውምም፤
ዘፍጥረት 45:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፤ በቤቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፣ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብጽ ምድር ላይ ገዥ አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፥ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፥ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፥ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብጽ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ። |
እንዲህም ብለው ነገሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕይወቱ ነው፤ እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፤ አላመናቸውምም፤
መጐናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፤ አክሊልህንም እሰጠዋለሁ፤ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩና በይሁዳም ለሚኖሩ አባት ይሆናል።
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢኣት አለበት” አለው።
ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፤ አባትና ካህንም ሁነኝ፤ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም ዐሥር ብር እሰጥሃለሁ” አለው።