Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 45:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አባታቸውንም፣ “እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብጽ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኗል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብም በድንጋጤ ክው አለ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ ዮሴፍ ገና በሕይወት ነው እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል። ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ አላመናቸውም ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 45:26
17 Referencias Cruzadas  

የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት።


ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም ወደ ያዕ​ቆብ ወደ ከነ​ዓን ምድር መጡ፤ የደ​ረ​ሰ​ባ​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ እን​ዲህ ብለው አወሩ፦


አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”


እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


አን​ዱም ከእኔ ወጣ፤ አውሬ በላው አላ​ች​ሁኝ፤ እስከ ዛሬም ገና አላ​የ​ሁ​ትም፤


እነ​ር​ሱም ከግ​ብፅ ሀገር ወጥ​ተው ሄዱ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ ያዕ​ቆብ ደረሱ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው።


በእ​ነ​ርሱ ብስቅ አያ​ም​ኑም፤ የፊ​ቴም ብር​ሃን አል​ወ​ደ​ቀም።


ብጠ​ራው፥ እር​ሱም ቢመ​ል​ስ​ልኝ ኖሮ፥ እንደ ሰማኝ አላ​ም​ንም ነበር።


ያዳ​ና​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ። ታላቅ ነገ​ር​ንም በግ​ብፅ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ካል​ሠራ፥ ቤትን የሚ​ሠሩ በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማን ካል​ጠ​በቀ፥ የሚ​ጠ​ብቁ በከ​ንቱ ይተ​ጋሉ።


እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤ አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።


ይህም ነገር በፊ​ታ​ቸው እንደ ተረት መሰ​ላ​ቸ​ውና አላ​መ​ኑ​አ​ቸ​ውም።


እን​ዲህ እያሉ፥ “ጌታ​ችን በእ​ው​ነት ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ለስ​ም​ዖ​ንም ታይ​ቶ​ታል።”


ከድ​ን​ጋጤ የተ​ነ​ሣም ገና ሳያ​ምኑ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ሲያ​ደ​ንቁ ሳሉ፥ “በዚህ አን​ዳች የሚ​በላ አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos