ዘፍጥረት 44:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉት፥ “ጌታችን እንደዚህ ለምን ክፉ ትናገራለህ? ይህን ነገር ያደርጉት ዘንድ ለባሪያዎችህ አግባባቸው አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን እንዲህ ያለ ነገር ለምን ይናገራል? እኛ አገልጋዮችህ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን እንዲህ ያለ ነገር ለምን ይናገራል? እኛ አገልጋዮችህ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ በማለት መልስ ሰጡት፤ “ጌታችን ሆይ፤ እንዴት እንዲህ ትናገራለህ? እኛ ይህን የመሰለ ነገር እንዳላደረግን በመሐላ እናረጋግጣለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉት፦ ጌታዬ እንደዚህ ያለው ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ያለውን ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ይህን ነገር የሚያደርጉ አይደሉም። |
እርሱም ሂዶ አገኛቸው፤ “ለምን እንዲህ አደረጋችሁ? ስለ አደረግሁላችሁ መልካም ነገር ለምን ክፉ ትከፍሉኛላችሁ? የጌታዬንስ የብር ጽዋ ለምን ሰረቃችሁኝ?” አላቸው።
በየዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር እንኳን ይዘን ከከነዓን ሀገር ወደ አንተ ተመልሰናል፤ ከጌታህስ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እንዴት እንሰርቃለን?
አዛሄልም፥ “ይህን ታላቅ ነገር አደርግ ዘንድ እኔ የሞተ ውሻ አገልጋይህ ምንድን ነኝ?” አለ። ኤልሳዕም፥ “አንተ በሶርያ ላይ ንጉሥ እንድትሆን እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው።