ዘፍጥረት 44:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለዚያም ብላቴናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባታችን እንዴት እሄዳለሁ? አባታችንን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? ፈጽሞ አላደርገውም፤ እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? ፈጽሞ አላደርገውም፤ እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁን ሳልይዝ እንዴት ወደ አባቴ መመለስ እችላለሁ? ይህን የመሰለ ከባድ ሥቃይ በአባቴ ላይ ሲደርስ ማየት አልችልም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለዚያም ብላቴናው ከእኔ ጋር ከሌለ ወደ አባቴ እንዴት እወጣለሁ? አባቴን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ። |
ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
እነሆ፥ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም” ያለቻቸውንም ነገር ለንጉሡ አስረዱት።
ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንደ አዳናቸው ለአማቱ ነገረው።