እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ዘፍጥረት 44:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እኔ በብላቴናው ፈንታ የጌታዬ አገልጋይ ሆኜ ልቀመጥ፤ ብላቴናው ግን ከወንድሞቹ ጋር ይሂድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ አሁን፣ አገልጋይህ በልጁ ፈንታ የአንተ የጌታዬ ባሪያ ሆኜ እዚሁ ልቅር፤ ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋራ ይመለስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አሁን፥ አገልጋይህ በልጁ ፈንታ የአንተ የጌታዬ ባርያ ሆኜ እዚሁ ልቅር፤ ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋር ይመለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እኔ በልጁ ፈንታ የአንተ የጌታዬ ባሪያ ሆኜ እዚሁ ልቅር፤ ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋር ይመለስ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም እኔ ባሪያህ በጌታዬ ዘንድ ባሪያ ሆኜ በብላቴናው ፋንታ ልቀመጥ ብላቴናውም ከወንድሞቹ ጋር ይውጣ። |
እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
እኔ አገልጋይህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዬ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ መልሼ በፊትህ ባላቆመው በአባቴ ዘንድ በዘመናት ሁሉ ኀጢአተኛ እሆናለሁ።
አለዚያም ብላቴናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባታችን እንዴት እሄዳለሁ? አባታችንን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።”
ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድያለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ተናገረው።