ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”
ዘፍጥረት 44:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ፤ እርሱም ገና ከዚያው ነበረ፤ በፊቱም በምድር ላይ ወደቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፣ እርሱ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም ከፊቱ መሬት ላይ ተደፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፥ እርሱ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም ከፊቱ መሬት ላይ ተደፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ሲመጡ ገና በቤት ሳለ አገኙት፤ ወደ መሬት ጐንበስ ብለው እጅ ነሡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ እርሱም ገና ከዚያው ነበረ፤ በፊቱም በምድር ላይ ወደቁ። |
ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”