La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 42:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእ​ነ​ርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ብራ​ቸ​ውን በዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ተቋ​ጥሮ አገ​ኙት፤ እነ​ር​ሱም አባ​ታ​ቸ​ውም የተ​ቋ​ጠረ ብራ​ቸ​ውን አይ​ተው ፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቾቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደ ተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቾቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደ ተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፥ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ እህላቸውን ከስልቾቻቸው ባራገፉ ጊዜ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ገንዘባቸውን እንደ ተቋጠረ አገኙ፤ እነርሱና አባታቸው የተመለሰውን ገንዘብ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በእየዓበታቸው ተቋጥሮ አገኙት እነርሱን አባታቸውም የብራቸውን ቍጥራት አይተው ፈሩ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 42:35
6 Referencias Cruzadas  

ብሩን በአ​ጠ​ፌታ አድ​ር​ጋ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ውሰዱ፤ በዓ​ይ​በ​ታ​ች​ሁም አፍ የተ​መ​ለ​ሰ​ውን ብር መል​ሳ​ችሁ ውሰዱ፤ ምና​ል​ባት ባለ​ማ​ወቅ ይሆ​ናል።


ሰዎ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ያችን እጅ መን​ሻና ብራ​ቸ​ውን በእ​ጥፍ፥ ብን​ያ​ም​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮ​ሴ​ፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፥ ወደ​ም​ና​ድ​ር​በ​ትም ስፍራ በደ​ረ​ስን ጊዜ ዓይ​በ​ታ​ች​ንን ከፈ​ትን፤ እነ​ሆም፥ የየ​አ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ብር በየ​ዓ​ይ​በቱ አፍ ነበር፤ አሁ​ንም ብራ​ች​ንን በእ​ጃ​ችን እንደ ሚዛኑ መለ​ስ​ነው።


ዮሴ​ፍም የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የእ​ነ​ዚህ ሰዎች ዓይ​በ​ቶ​ቻ​ቸው መያዝ የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል እህል ሙላ​ላ​ቸው፤ የሁ​ሉ​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው አፍ ጨም​ረው፤


በእጁም የወርቅ ከረጢት ይዞአል፤ ወደ ቤቱ ቢመለስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው።”