La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 42:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ሰላ​ማ​ው​ያን እንጂ ሰላ​ዮች አለ​መ​ሆ​ና​ች​ሁ​ንም በዚህ ዐው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሀ​ገ​ራ​ችን ትነ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።’ ”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያም ጊዜ ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደ ልብ ለመዘዋወር ትችላላችሁ።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያንም ጊዜ ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደ ልብ ለመዘዋወር ትችላላችሁ።’”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታናሽ ወንድማችሁንም ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት ታማኞች ሰዎች መሆናችሁንና ሰላዮችም አለመሆናችሁን አረጋግጣለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ በዚህም አገር ቈይታችሁ እንደ ፈለጋችሁ መነገድ ትችላላችሁ።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ እውነተኞች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ አውቀዋለሁ ወንድማችሁንም እሰጣችኍለሁ እናንተም በምድሩ ትነግዳላችሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 42:34
7 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እነሆ፥ ምድሬ በፊ​ትህ ናት፤ በወ​ደ​ድ​ኸው ተቀ​መጥ።”


ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።”


“እነ​ዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰ​ላም ሰዎች ናቸው፤ በም​ድ​ራ​ችን ይቀ​መጡ፤ ይነ​ግ​ዱ​ባ​ትም፤ እነ​ሆም፥ ምድ​ሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ው​ሰድ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ስጥ።


ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከአ​ላ​መ​ጣ​ችሁ በቀር ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ከዚህ አት​ወ​ጡም።


ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገ​ራ​ችሁ የታ​መነ ይሆ​ና​ልና፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ግን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ።


ይኽ​ንም፥ ግብር የሚ​ያ​ስ​ገ​ብሩ ሰዎች፥ ነጋ​ዴ​ዎ​ችም፥ በዙ​ሪ​ያው ያሉ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ፥ የም​ድ​ርም ሹሞች ከሚ​ያ​ወ​ጡት ሌላ ነው።


ቀን​በ​ጡ​ንም ቀነ​ጠበ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ወሰ​ደው፤ ቅጥር ባለው ከተ​ማም አኖ​ረው።