ዘፍጥረት 42:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ዮሴፍ ነገራቸውን እንደሚሰማባቸው አላወቁም፤ በመካከላቸው አስተርጓሚ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለ ሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማቸው አላወቁም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለ ሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማቸው አላወቁም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ እነርሱ የሚሉትን ሁሉ ያዳምጥ ነበር፤ እነርሱ ግን ከዮሴፍ ጋር የሚነጋገሩት በአስተርጓሚ ስለ ነበር የእነርሱን ንግግር ዮሴፍ እንደሚሰማቸው አላወቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ዮሴፍ ነገራቸውን እንደሚስማባቸው አላወቁም በመካከላቸው አስተርጓሚ ነበረና። |
ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ብላቴናውን አትበድሉ ብዬአችሁ አልነበረምን? እኔንም አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈላለጋችኋል።”
ዮሴፍም ከእነርሱ ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ደግሞም ወደ እነርሱ ተመልሶ ተናገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ወስዶ በፊታቸው አሰረው።
እነሆም፥ ለእናንተ እኔ ራሴ በአፌ እንደ ተናገርሁአችሁ እናንተ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ወንድሜ ብንያም በዐዓይኖቹ አይቶአል።
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።