ዘፍጥረት 41:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩም ፈርዖንንና ሰዎቹን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕቅዱም ለፈርዖንና ለባለሟሎቹ ሁሉ መልካም ሆኖ ታያቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩም በፈርዖንና በሎሌዎቹ ፊት መልካም ሆነ፤ |
ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፥ “በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰውን እናገኛለን?”
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።
ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት የእስራኤል መሳፍንት ሁሉ ፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰኛቸው።