ዘፍጥረት 41:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በኋላ እነሆ የሰለቱና በነፋስ የተመቱ ሌሎች ሰባት እሸቶች ወጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ ሰባት የእሸት ዛላዎች ታዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በኍላ እነሆ የደረቁና የሰለቱ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ስባት እሸቶች ወጡ |
እነዚያ የሰለቱትና በነፋስ የተመቱት እሸቶች እነዚያን ያማሩትንና የጐመሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ፤ የተረጐመልኝም የለም።”
ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጆቻቸው ዝለዋል፤ ደንግጠውም አፍረዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል።
ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
ነፋስን ዘርተዋልና ዐውሎ ነፋስን አጨዱ፤ ለነዶአቸውም ኀይል የለውም፤ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም ጠላት ይበላዋል።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።