La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 40:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም፥ “ሕል​ምን አል​መን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ልን አጣን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ሕል​ምን የሚ​ተ​ረ​ጕም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እስቲ ንገ​ሩኝ፤ ሕል​ማ​ችሁ ምን​ድን ነው?”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጕምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለምን? እስኪ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፥ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለምን? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም “እያንዳንዳችን ሕልም አየን፤ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን ሕልም የሚተረጒም ማንም የለም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልም የመተርጐም ችሎታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም፦ ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን አሉት ዮሴፍም አላቸው፦ ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 40:8
17 Referencias Cruzadas  

የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ ሕል​ሙን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “በሕ​ልሜ የወ​ይን ሐረግ በፊቴ ሆና አየሁ፥


ዮሴ​ፍም ፈር​ዖ​ንን አለው፥ “የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​ይ​ቶ​ታል።


የሞት መላ​እ​ክት ምንም ሺህ ቢሆኑ፥ በልቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊመ​ለስ ቢያ​ስብ፥ ኀጢ​አ​ቱን ለሰው ቢና​ገር፥ በደ​ሉ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ከእ​ነ​ርሱ አንዱ እንኳ አይ​ገ​ድ​ለ​ውም፤


እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።