ዘፍጥረት 40:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስር ቤቱ ዘበኞች አለቃም ለዮሴፍ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ያገለግላቸው ነበር፤ በግዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ ዮሴፍም በሚያስፈልጋቸው ይረዳቸው ነበር። እስር ቤት ገብተው ጥቂት እንደ ቈዩም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ ዮሴፍም በሚያስፈልጋቸው ይረዳቸው ነበር። እስር ቤት ገብተው ጥቂት እንደቈዩም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስር ቤቱም አዛዥ ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ ዮሴፍም ያገለግላቸው ነበር። በእስር ቤትም ለጥቂት ጊዜ ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ለዮሴፍ አሳልፎ ሰጣቸው እርሱም ያገልግላቸው ነበር በግዞት ቤትም አያሌ ቀን ተቀመጡ። |
ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የመጋቢዎቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ከአወረዱት ከይስማኤላውያን እጅ ገዛው።
ሁለቱም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለሙ። በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ሁለቱም እየራሳቸው ሕልምን አለሙ።