ዘፍጥረት 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም “ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ” አለች። ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደችው። አቤልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየልም ምድርን የሚያርስ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ፣ ቃየንም ዐራሽ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፥ ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፥ ቃየንም መሬትን የሚያርስ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም የቃየልን ወንድም አቤልን ወለደች፤ አቤል የበጎች ጠባቂ ሆነ፤ ቃየል ግን ገበሬ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፤ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበረ። |
እስራኤልም ዮሴፍን፥ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና” አለው። እርሱም፥ “እሺ” አለው።
ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች፥ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፥ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አባታችንም ከብት ጠባቂዎች ነን” አሉት።
ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ በጎቹንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ገደሉት እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ እውነት እላችኋለሁ ከዚች ትውልድ ይፈለጋል።
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።
ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።