La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 39:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ የመ​ጋ​ቢ​ዎ​ቹም አለቃ የሚ​ሆን የግ​ብፅ ሰው ጲጥ​ፋራ ወደ ግብፅ ከአ​ወ​ረ​ዱት ከይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እጅ ገዛው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብጻዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፥ ግብፃዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስማኤላውያን ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት፤ እዚያም ከግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ ለሆነው ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር የተባለው ግብጻዊ፥ የፈርዖን የዘበኞች አለቃ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ዺጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላዉያን እጅ ገዛው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 39:1
7 Referencias Cruzadas  

እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።


እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።


እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ሰዎች ግን ዮሴ​ፍን በግ​ብፅ ለፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ ለዘ​በ​ኞቹ አለቃ ለጲ​ጥ​ፋራ ሸጡት።


በእ​ስር ቤት ውስ​ጥም ዮሴፍ ታስሮ በነ​በ​ረ​በት የግ​ዞት ስፍራ አጋ​ዛ​ቸው።


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ወደ እር​ሱም ቀረቡ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸ​ጣ​ች​ሁኝ እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ።


ምድር ተከ​ፈ​ተች፥ ዳታ​ን​ንም ዋጠ​ችው፥ የአ​ቤ​ሮ​ን​ንም ወገን ደፈ​ነች፤


“የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችም በዮ​ሴፍ ላይ ቀን​ተው ወደ ግብፅ ሀገር ሸጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።