ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ዘፍጥረት 38:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስትወልድም አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰረች፥ “ይህ መጀመሪያ ይወጣል” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፥ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትወልድበትም ጊዜ ከመንትያዎቹ አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ሴት ቀይ ክር በእጁ ላይ አሰረችለትና “ይህ በመጀመሪያ ወጣ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስትውልድም አንድ እጁን አወጣ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አስረች፦ ይህ መጀመሪያ ይወጣል አለች። |
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።