እርስዋም የመበለትነቷን ልብስ አወለቀች፤ መጐናጸፊያዋንም ለበሰች፤ ተሸፈነችም፤ ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስትም ትሆነው ዘንድ እርስዋን ሊሰጠው እንዳልፈለገ አይታለችና።
ዘፍጥረት 38:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞትብኝ ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት። ይህን ያለውም፣ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፥ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴላ እስከሚያድግበት ጊዜ ድረስ ሂጂና በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ኑሪ” አላት። ይህንንም ያለው እንደ ወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሰጋ ነበር፤ ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም ምራትን ትዕማርን፦ ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ አላት እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞት ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባትዋ ቤት ተቀመጠች። |
እርስዋም የመበለትነቷን ልብስ አወለቀች፤ መጐናጸፊያዋንም ለበሰች፤ ተሸፈነችም፤ ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስትም ትሆነው ዘንድ እርስዋን ሊሰጠው እንዳልፈለገ አይታለችና።
የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነቷ እንደ ነበረች ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ፥ ከአባቷ እንጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ።