Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 38:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዘመ​ን​ዋም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ የይ​ሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁ​ዳም ተጽ​ናና፤ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ወደ​ሚ​ሸ​ል​ቱት ሰዎ​ችም ወደ ተምና ወጣ፤ እር​ሱም ዓዶ​ሎ​ማ​ዊው በግ ጠባ​ቂው ኤራ​ስም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከኤራ ጋራ የበጎቹን ጠጕር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከብዙ ዘመንም በኍላ የይሁዳ ሚስት የሴዋ ልጅ ሞተች ይሁዳም ተጽናና የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ እርሱም ዓዶሎማዊው ወዳጁም ኤራስ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 38:12
13 Referencias Cruzadas  

ድን​በ​ሩም ከበ​ኣላ በባ​ሕር በኩል ያል​ፋል፤ ከዚ​ያም በኢ​ያ​ሪም ከተማ ደቡብ በኩ​ልና በኪ​ስ​ሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥ​ራ​ቱስ ድን​በር ያል​ፋል፤ በፀ​ሐይ ከተ​ማም ላይ ይወ​ር​ዳል፤ በሊ​ባም በኩል ያል​ፋል።


ንጉ​ሡም ዳዊት አቤ​ሴ​ሎ​ምን መከ​ታ​ተ​ልን ተወ፤ ስለ ሞተው ልጁ ስለ አም​ኖን ተጽ​ና​ንቶ ነበ​ርና።


ሶም​ሶ​ንም ወደ ቴም​ናታ ወረደ፤ በቴ​ም​ና​ታም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልጆች አን​ዲት ሴት አየ፤ እር​ስ​ዋም በፊቱ ደስ አለ​ችው።


ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።


አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።


ኤሎን፥ ቴም​ናታ፥ አቃ​ሮን፥


ጋባ፥ ተምና፥ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ሴና፥ አዳ​ሶን፥ ማጋ​ዳ​ል​ጋድ፤


ኤር​ሙት፥ ኤዶ​ላም፥ ሜም​ብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤


በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ተለ​ይቶ ወረደ፤ ስሙ ኤራስ በሚ​ባል በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊ​ውም ሰው ዘንድ አደረ።


ላባ ግን በጎ​ቹን ለመ​ሸ​ለት ሄዶ ነበር፤ ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ሰረ​ቀች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios