ዘፍጥረት 36:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የቴማኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮባብም ሞተ፥ በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሻም ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮባብም በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ተወላጅ ሑሻም በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ |
የዔሳው ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስፍን፥ ኦሜር መስፍን፥ ሳፍር መስፍን፥ ቄኔዝ መስፍን፥
ሑሳምም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የገደለ የቤዳድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማዋም ስም ዓዊት ተባለ።
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።
ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ፤ ከቴማንና ከድዳንም ያመለጡ በሰይፍ ይወድቃሉ።