ዘፍጥረት 36:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይስማኤልን ልጅ የናቡአት እኅት ቤሴሞትን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስማኤልን ልጅ የነባዮትን እኅት ባሴማትን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነባዮት እኅት የነበረችው የእስማኤል ልጅ ባሴማት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስማኤልን ልጅ የነባዮትን እኅት ቤሴሞትን። |
ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ዔሳው ወደ ይስማኤል ሄደ፤ ቤሴሞትንም በፊት ካሉ ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ ወሰዳት፤ እርስዋም የናኮር ወንድም የአብርሃም ልጅ የሆነው የይስማኤል ልጅና የናቡዓት እኅት ናት።
ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥