ዘፍጥረት 36:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሪሶን ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዑሳ፥ አራን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዲሳን ወንዶች ልጆች፦ ዑፅ እና አራን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዲሻን ልጆች ዑፅና አራን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዲሻን ልጆች ዑፅና አራን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዲሳን ልጆችም እነዚህ ናቸው ዑፅ አራን። |
አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፤ አስቀሎናንም፥ ጋዛንም፥ አቃሮንንም፥ የአዛጦንንም ቅሬታ፤
ሣን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሤትም አድርጊ፤ የእግዚአብሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋልና፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ፥ ትራቆቻለሽም።