La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 35:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዕ​ቆ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር በተ​ነ​ጋ​ገ​ረ​በት ቦታ የድ​ን​ጋይ ሐው​ልት ተከለ፤ የመ​ጠጥ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በእ​ርሱ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ዘይ​ት​ንም አፈ​ሰ​ሰ​በት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያዕቆብም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ ዘይትንም አፈሰሰበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያዕቆብም፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ መታሰቢያ የሚሆን የተቀደሰ ዐምድ አቆመ፤ የወይን ጠጅና ዘይት በላዩ አፈሰሰበት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ ዘይትንም አፈሰሰበት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 35:14
6 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አቆመ።


ያዕ​ቆ​ብም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ላይ ሐው​ልት አቆመ፤ እር​ስ​ዋም እስከ ዛሬ የራ​ሔል የመ​ቃ​ብ​ርዋ ሐው​ልት ትባ​ላ​ለች።


ሦስ​ቱም ኀያ​ላን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ሰን​ጥ​ቀው ሄዱ፤ በበ​ሩም አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘ​ውም ለዳ​ዊት አመ​ጡ​ለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፈ​ሰ​ሰው።


ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን” ብሎ ጠራው፤


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።