ዘፍጥረት 34:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፤ ብላቴናዪቱንም ወደዳት፤ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሱም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈች፥ ልጅቱንም አፈቀራት፥ እርሷንም በአፍቅሮት አናገራት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውበቷ ተማርኮ እጅግ ወደዳት፤ እርስዋም እንድትወደው ለማድረግ በፍቅር ቃል አነጋገራት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ ብላቴናይቱንም ወደዳት ልብዋንም ደስ በሚያስኛት ነገር ተናገራት። |
አሁንም አትፍሩ፤ እኔ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን እመግባችኋለሁ።” አጽናናቸውም፤ በልባቸው የሚገባ ነገርም ነገራቸው።
አሁንም ተነሥተህ ወጥተህ ለአገልጋዮችህ በልባቸው የሚገባ ነገር ንገራቸው። ዛሬ ወደ እነርሱ ካልወጣህ በዚች ሌሊት አንድ ሰው ስንኳ ከአንተ ጋር የሚያድር እንዳይኖር በእግዚአብሔር እምላለሁ፤ ከሕፃንነትህ ጀምሮ እስከዚች ቀን ድረስ ካገኘህ መከራ ሁሉ ዛሬ የምታገኝህ መከራ እንድትከፋብህ እንግዲህ አንተ ለራስህ ዕወቅ” አለው።
ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያንን ሁሉ ያጽናና ነበር። የደኅንነትም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
ባልዋም ተነሣ፤ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር አንድ ብላቴና፥ ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብላቴናዪቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀበለው።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳኦል መንገሩን በፈጸመ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፤ ዮናታንም እንደ ነፍሱ ወደደው።